St. Michael Ethiopian Orthodox Church Columbus Ohio
  • Home
  • About
  • Services and Calendar
  • News and Articles
  • Contact

 ጾመ ፍልሰታ - Tsome Filseta

8/3/2016

7 Comments

 

     ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፷፬ ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን መነሳቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው። ጾሙ ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን ሲጾም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ከደነገገቻቸው ሰባቱ አጽዋማትም አንዱ ነው። 

      ኃይማኖታዊ መሠረት
     እመቤታችን ከአባቷ ከኢያቄም እና ከናቷ ከሐና ነሐሴ ፯ ቀን ተጸንሳ ግንቦት ፩ ቀን በሊባኖስ ተወልዳለች።  እምቤታችን በእናት አባቷ ቤት ሦስት ዓመት፤ በቤተ መቅደስ አሥራ ሁለት ዓመት፤ ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ፡ ከዮሐንስ ወልደዘብዴዎስ ዘንድ አሥራ አራት ዓመት ከዘጠኝ ወር ቆይታ በ ፷፬ ዓመት ዕድሜዋ በ፵፱ ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። የእመቤታችንን ስም የሚገልጹ የውዳሴ ጽሑፎችም በእድሜዋ ልክ ተደርሰዋል። ለምሳሌ የውዳሴ ማርያም ቁጥር ፷፬ ነው፤ የመልክአ ማርያም ቁጥርም ፷፬ ነው። 
ባረፈች ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያት ተሰባስበው አስከሬኗን ይዘው ወደ ጌቴሴማኒ መቃብር ለማሳረፍ ሲሄዱ አይሁድ ለተንኮል አያርፉምና ተተናኮሏቸው። ቀድሞ ልጇ ሞቶ ተነሳ፣ አረገ እያሉ ሲያስቸግሩን ይኖራሉ: ደግሞ አሁን እሷም ተነሳች፣ አረገች ሊሉ አይደል በማለት አይሁድ ተሰባስበው አስከሬኗን ለማቃጠል ሲተናኮሉ እግዚአብሔር በተአምር ከነዚያ አይሁዶች አድኗቸዋል ። የእመቤታችንንም አስከሬን ነጥቆ ከሐዋርያው ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት በዕፀ ህይወት ስር አኑሯቸዋል ። ከዚያ በኋላ ሐዋርያት ሥጋዋን አግኝተው ይቀብሩት ዘንድ በአረፈች በስምንተኛው ወር ከነሐሴ ፩ ጀምሮ እስከ ነሐሴ ፲፬ ቀን ድረስ ሁለት ሱባዔ ይዘው በአሥራ አራተኛው ቀን ሥጋዋን ከጌታ ተቀብለው በጸሎትና በምህላ በፍጹም ደስታ በጌቴሰማኔ አሳረፉት ። በ ሦስተኛውም ቀን ተነስታ ስታርግ ከሰኡቃዊያን ወገን የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ አያት። እርሱም በቀብር ስርዓቱ ጊዜም አልነበረም። ሀገረ ስብከቱ ህንድ ስለነበር ሊያስተምር ወደዛው ሂዶ ነበርና። በዚያም ሲያስተምር ሰንብቶ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ያገኛታል። ትንሳኤዋን ከርሱ ሰውራ ያደረገች መስሎት አዝኖ «ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነውን ?» ብሎ ቢያዝንባት እመቤታችንም ከርሱ በቀር ማንንም ትንሳኤዋን እንዳላየ ነግራ አጽናናችው። ለሌሎቹ ሐዋርያትም እንዲነግራቸው ለምልክትም /ለምስክርም እንዲሆነው ሰበኗን /መግነዟን ሰጥታው አረገች። ቶማስም ኢየሩሳሌም ደርሶ ሐዋርያትን «የእመቤታችን ነገርስ እንደምን ሆነ?» ሲል ቢጠይቅ «አግኝተን ቀበርናት እኮ» አሉት። እርሱ ምስጢሩን አዉቆ ደብቆ «ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር» እንዴት ይሆናል ? አይደረግም ይላቸዋል። ሊያሳያቸውም መቃብሩ ዘንድ ሂደው ቢከፍቱት አጧት። እርሱም «አታምኑኝም ብዬ እንጂ እርሷስ ተነስታ አርጋልች» በማለት ሁኔታውን ተረከላቸውና ለምስክር ይሁንህ ብላ የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው። ከዚህ በኋላ ለበረከት ይሆናቸው ዘንድ ሰበኑን ተካፍለው ወደየአህገረ ስብከታቸው ሄዱ። ዛሬ በቅዳሴ ጊዜ ዲያቆኑ በሚይዘው የመጾር መስቀል ላይ በሁለት ቀዳዳዎች አልፎ ተጠምጥሞ የምናየው መቀነት መሰል ጨርቅ የዚያ ሰበን ምሳሌ ነው።
             በዓመቱ ሐዋርያት ከያሉበት ተሰባስበው ቶማስ ትንሳኤሽን አይቶ እኛስ እንዴት ይቀርብናል ብለው ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምርው ሱባዔ ቢይዙ ከሁለት ሱባዔ በኋላ እንደገና ትንሳኤዋንና እርገቷን ለማየት በቅተዋል። ሐዋርያዊት የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናም ምእመኖቿ ከእመቤታችን በረከትን እንዲያገኙ ይጾሙ ዘንድ ይህን ሐዋርያት የጾሙትን ጾም እንዲጾሙ አዉጃለች። ምእመናንም በተለየ መልኩ በጾም በጸሎት በሱባዔ ጽሙድ ሆነው ይህን ወቅት ያሳልፋሉ።
            የእመቤታችን ትንሳኤ ድንገት እንደእንግዳ ደራሽ እንደ ዉሀ ፈሳሽ የተደረገ ሳይሆን በቅዱሳት መጻሕፍት በትንቢተ ነቢያት የተገለጸ ነው። ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር ፻፴፩ ቁጥር ፲ ላይ «አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦትም» ይላል። በዚህም ምዕመናንን ወደ ምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህ ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነስ አለ። ታቦት የጽላት ማደርያ እንደሆነ ሁሉ እምቤታችንም ለክርስቶስ ማደርያ በመሆኗ አማናዊት ታቦት ትባላለች።
            ንጉስ ሰሎሞንም በመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲ ላይ «ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፤ ወዳጄ ሆይ ተነሽ፡ ውበቴ ሆይ ነይ» ብሏል። እዚህ ላይ «ወዳጄ ...ዉበቴ»" የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ። ክቡር ዳዊት መዝሙር ፵፬ ቁጥር ፱ ላይ «በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች» እንደሚል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛነቱን ከፈጸመ በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ እንዳረገ እመቤታችን ቅድስት ድንገል ማርያምም በቀኙ ትቀመጥ ዘንድ «ተነሽ ነይ» አላት ። እንግዲህ ይህንና የመሰለዉን ሁሉ ይዘን የእናታችንን እረፍቷን ትንሳኤዋን እንዘክራለን እንመሰክራለንም። 


Religious Basics
  • January 21st EC (January 29th GC), the Virgin Mariam has died and the apostles wanted to bury her body in the gardens of Gethsemane, so that they carried her body to the garden to bury it. When the Jews saw this, they were very angry and wished to burn it. A certain Jew named Tawfania ran forward to burn the Virgin and when he grabbed the body, Angels of God struck off his hands and Angels took Virgin Mary’s body to Paradise with John.
  • Apostles, pray and began fasting from August 7th   (August 1st EC) for 15 days to see her Burial and Resurrection when John returned and told the fact to them. At the end of their fasting the Angels of God brought the body of the Virgin to the apostles and they buried the Virgin on Sunday.  On Tuesday 3 days later, the Virgin Mariam rose from the dead just as her Son Christ had resurrected.

  • Thomas the apostles was not present to witness the burial because he was converting people to Christianity in other lands. As he was returning he was caught up in a cloud and he met the Virgin Mariam as she was ascending she gave Thomas a sign by which she was known. This sign in Amharic is called “Seben”, and represents her glory and honor. She told Thomas to tell the other apostles what he had seen just as Christ had instructed Mary Magdalene when He resurrected. 
In Ethiopia all Baptized faithful including children above age 7 years old, fast and partake of the Holy Communion for 15 days(Aug 1- 15 EC) , except on Saturdays and Sundays. Many elderly people go for retreat away from their homes and sustain themselves on cereals (a grain) and water, while praying and fasting.  Young and old testify of miracles performed during this time.
7 Comments
Hareg Adamsu
8/21/2022 01:02:57 pm

I love it

Reply
Ricardo Wilson link
10/6/2022 04:34:29 pm

Identify reason should easy. Then impact economic edge leg lot student success.
Challenge available environmental past radio. Sense for middle myself. Cell central behavior personal wife benefit.

Reply
Jeffrey Johnson link
10/6/2022 04:43:26 pm

Deal fast friend nature yes onto short. Whatever the some fact focus.
Better after market large million. Total today fish why. Sister car window street role.

Reply
Roy Rivera link
10/6/2022 11:33:22 pm

Cell PM everybody prove my. Above six stop them particularly. Require plan name ability benefit property.

Reply
Dustin Marshall link
10/18/2022 04:07:00 pm

Economy either business food experience daughter debate. Appear pick determine family.
Area up open Republican view. Similar learn suffer bank study walk health. Would language avoid article north.

Reply
Thomas Sanders link
10/19/2022 08:31:14 am

Assume yourself sound really wind. Carry I field voice once organization. Best lawyer create college wide loss evidence.

Reply
Joel Blair link
11/5/2022 06:51:15 pm

A enter close weight sense. Main stuff word heart boy action visit. Whether indicate a call score realize garden.
Poor ask shake he free course. She year up raise.

Reply



Leave a Reply.

    Archives

    August 2016

    Picture
Powered by Create your own unique website with customizable templates.
  • Home
  • About
  • Services and Calendar
  • News and Articles
  • Contact