St. Michael Ethiopian Orthodox Church Columbus Ohio
  • Home
  • About
  • Services and Calendar
  • News and Articles
  • Contact

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት መሰረት

7/19/2016

1 Comment

 
ከኒቂያ ጉባኤ
​ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።

 ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፤ የተፈጠረ ያይደለ የተወለደ፤ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል። ሁሉ በእርሱ ሆነ ያለ እርሱ ምንም ምን የሆነ የለም፤በሰማይም ያለ በምድርም ያለ። ስለ እኛ ስለ ሰዎች ስለመዳናችን ከሰማይ ወረደ። በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ። ሰው ሆኖ በጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለእኛ ተሰቀለ፤ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ። በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ።ዳግመኛም ሕያዋንንና ሙታንንምይገዛ ዘንድ በጌትነት ይመጣል።ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።

       ጌታ ማኅየዊ በሚሆን ከአብ በሰረፀ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን፤ እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና ከወልድ ጋር በነቢያት የተናገረ።

        ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰብዋት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን። ኃጢአትን ለማስተሥረይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን። የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን። የሚመጣውንም ሕይወት ለዘለዓለሙ አሜን። 

Nicene-Constantinopolitan Creed
We believe in one God, the Father Almighty, Maker of heaven and earth, and of all things visible and invisible.

And in one Lord Jesus Christ, the Son of God, the only-begotten, begotten of the Father before all ages. Light of Light; true God of true God; begotten, not made; of one essence with the Father, by whom all things were made; who for us men and for our salvation came down from heaven, and was incarnate of the Holy Spirit and the Virgin Mary, and became man. And He was crucified for us under Pontius Pilate, and suffered, and was buried. And the third day He rose again, according to the Scriptures; and ascended into heaven, and sits at the right hand of the Father; and He shall come again with glory to judge the living and the dead; whose Kingdom shall have no end.

And we believe in the Holy Spirit, the Lord, the Giver of Life, who proceeds from the Father; who with the Father and the Son together is worshipped and glorified; who spoke by the prophets.

​ We believe In one Holy,  Apostolic Church. We acknowledge one baptism for the remission of sins. We look for the resurrection of the dead, and the life of the world to come. 
​Amen
1 Comment
Virginia Home Designer link
3/13/2023 04:39:19 am

Good reeading

Reply



Leave a Reply.

Powered by Create your own unique website with customizable templates.
  • Home
  • About
  • Services and Calendar
  • News and Articles
  • Contact